ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ፤ በ2012 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአዲስ አበባ አዳማ እና በድሬዳዋ ከገነባቸው የክፍያ መንገዶች ከ298 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡
ኢንተርፕራይዙ ገቢውን ያገኘው በአዲስ-አዳማ፣ በድሬዳዋ-ደወሌ የክፍያ መንገዶች ባስተናገዳቸው ተሸከርካሪዎች፤ ከክፍያ መንገድ አገልግሎት ከ274 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ አድርጓል።
ድርጅቱ ከልዩ ልዩ ገቢዎች ማለትም ከማስታወቂያ ቦታዎች ኪራይ፣ ከተሽከርካሪ ማንሳት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ከ23 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከ298 ሚሊየን ብር በላይ ከክፍያ መንገዱ ገቢ መሰብሰቡ ታውቋል::