ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ግብፅ ከዓለም ዐቀፉ የገንዘብ ተቋም የ2.77 ቢሊየን ዶላር ብድር እንደፀደቀላት ተነገረ። ተቋሙ ሀገራት ኮሮና ወረርሽኝ እያደረሰባቸው ካለው የኢኮኖሚ ጉዳት ለማንሰራራት የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ በዘረጋው ፕሮግራም ነው ለግብፅብድሩን ለመስጠት ፍቃደኝነቱን ያሳየው።
ግብፅ ኢኮኖሚዋ ላይ የጀመረችው ማሻሻያ ፈተና ገጥሞታል ያሉት የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ዳይሬክተር ጂኦፍሬይ ኦካምቶ ናቸው። የክፍያ ሚዛን ጉድለቱና መዛባቱም ከዋናዎቹ የኢኮኖሚ ራስ ምታቷ መንስዔዎች ናቸው ብለዋል። ግለሰቡ ይህን ይበሉ እንጂ ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ሳቢያ ወደ ግጭትና ጦርነት ለመግባት ሽር ጉድ እያለች መሆኑ ይታወቃል::
ግብፅ የኮሮና ወረርሽኝ ከፍተኛ ጫና ካስከተለባቸው የአፍሪካ ሀገራት አንዷ ናት። አይ ኤም ኤፍ ካለፈው አንድ ወር ወዲህ ለአፍሪካ ሀገራት እየሰጠ ካለው ብድር መጠንን ሰንጠረዡ እንደሚያሳየው ከሆነ ናይጄሪያ፣ ግብፅ እና ጋና በቅደም ተከተል በአንፃራዊነት ከፍተኛ ገንዘብ ያገኙ ሀገራት በመሆን ተመዝግበዋል።