በቤታቸው እንዲሠሩ የታዘዙ የመንግሥት ሠራተኞች ትራንስፖርት ሲጠቀሙ ከተገኙ መታወቂያቸው ይቀማል ተባለ

በቤታቸው እንዲሠሩ የታዘዙ የመንግሥት ሠራተኞች ትራንስፖርት ሲጠቀሙ ከተገኙ መታወቂያቸው ይቀማል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በኮሮና ቫይረስ ስጋት በመንግሥት ከቤታቸው ሆነው ሥራ እንዲሠሩ የተደረጉ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲጠቀሙ ከተገኙ መታወቂያቸውን እንደሚነጠቁ ተነገረ፡፡

ከፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ጋር በመተባበር ቢሮ  ገብተው እንዲሠሩ ከተፈቀደላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ውጭ ፤ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ሠራተኞች ከተገኙ የትራንስፖርት መጠቀሚያ መታወቂያቸውን እሰከ ወዲያኛው ሊነጠቁ ይችላል ነው የተባለው።

መንግሥት ያለውን መጨናነቁን ለመቀነስ የፌደራልና የአዲስ አበባ የመንግሥት ሠራተኞች የተለያየ የመውጫና መግቢያ ሰዐት በማስቀመጥ ፤ መገፋፋቱን ለመቀነስ ጥረት አድርጓል:: በመሆኑም ቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ የተወሰነ ሠራተኞች በቤታቸው በመወሰን ሥራቸውን መከወን እንዳለባቸው መንግሥት ዛሬ አሳስቧል፡፡

ይህን መመሪያ ተከትሎ ቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ የተደረጉ የፌደራል ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች በፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎቱ በመታወቂያቸው መጠቀም አይችሉም ተብሏል።

ከዚህ ቀደም ተግባራዊ በተደረገው የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዐት ማሻሻያ መሰረት የፌደራል መንግሥት ሠራተኞች ጠዋት 1፡30 የሥራ ቦታቸው የሚደርሱ ሲሆን  ፤ የአዲስ አበባ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ደግሞ ጠዋት 2፡00 በመነሳት ከረፋዱ 3፡30 ወደ ሥራ  እንደሚገቡ መመሪያ መውጣቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY