የመብራት ለመክፈል ንግድ ባንክ ከፍተኛ ወረፋ ተጨናንቋል 

የመብራት ለመክፈል ንግድ ባንክ ከፍተኛ ወረፋ ተጨናንቋል 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ክፍያን በተመለከተ አዲስ አሠራር ዘርግቻለሁ ያለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ስምምነት ቢፈጽምም በሁሉም ንግድ ባንክች ከፍተኛ የሆነ መጨናነቅ እየታየ ነው ተባለ::

በወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ወቅት ተጠቃሚዎች የሚያደርስባቸው እንግልት ለመቀነስ በሚል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል መሰብሰብ ከጀመረ ሰንበትበት ቢልም፤ በባንኩ ቅርንጫፎች የኤሌክትሪክ ሒሳብ ለመክፈል ያለው መጨናነቅ በታሰበው መጠን ከመቀነስ ይልቅ ከፍተኛ ግርግርና ወረፋን አስከትሏል፡፡

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች የሚታየውን ረዣዥም ሰልፎች ተከትሎ በመዲናዋ የተለያዮ ስፍራዎች ተዘዋውሮ ነዋሪዎችን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን የወረፋዎቹ ዋነኛ መንስዔ የኤሌኬትሪክ ወርሀዊ ክፍናውች መሆናቸውን መረዳት ችሏል::

ይህ አሠራር ከከኮሮና ቫይረስ ርቀትን የመጠበቅ አሠራር ጋር ተዳምሮ መደበኛ የባንክ አገልግልት ተጠቃሚዎችም ላይ ችግር ሊፈጥር ችሏል ነው ያሉት ተገልጋዮቹ::

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የቅድመ ክፍያ የካርድ አገልግሎትን በሱቆች እና በሱፐር ማርኬቶች ደረጃ ለመስጠት ዕቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑንና ይህ አማራጭ መንገድ በቅርብ ጊዜ በተግባር ላይ እንደሚውል ለመ/ቤቱ ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮች ነግረውናል፡፡

LEAVE A REPLY