8 ዓይነት የኮሮና ክትባት መድኃኒቶች በፍጥነት እየተሠሩ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድርስ አድኃኖም ገለፁ

8 ዓይነት የኮሮና ክትባት መድኃኒቶች በፍጥነት እየተሠሩ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድርስ አድኃኖም ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በዶክተር ቴዎድሮስ  አድኃኖም የሚመራው የዓለም የጤና ድርጅት 7 ወይንም 8 የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድኃኒት እዉን ለማድረግ በፍጥነት እየተሠራ መሆኑን ገለፁ::

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ምክር ቤት ጋር በቪዲዮ በነበራቸዉ ዉይይት ላይ 7 ወይንም 8 የሚሆኑ የቫይረሱ የክትባት መድኃኒት በእጩነት በመምረጥ የምርምር ሥራዉ ተጠናክሮ መቀጠሉን አረጋግጠዋል፡፡

ባሳለፍነዉ ሳምንት ከ40 የዓለም ሀገራት፣ ተቋማትና ባንኮች ለክትባቱ፣ ለምርምር ሥራ በተለገሰዉ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ሥራዉ የሚከናወን ሲሆን ፤ ተጨማሪ ፈንድ እንደሚያስፈልግ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አስረድተዋል፡፡

ለኮሮና ቫይረስ ክትባት በሚል ከ100 በላይ እጩ የምርምር ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን፤ ከእነርሱም መካከል እጅግ የተሻሉ ናቸው የተባሉ  ስምንት ያህሉ መለየታቸዉን የዓለም የጤና ደርጅት ቢጠቁምም ፤ ተለዩ ስለተባሉት የክትባት መድኃኒት ዓይነቶች ዝርዝር  መረጃ ግን አልሰጠም፡፡

የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ከስልጣን መልቀቅ አለባቸው ስትል አሜሪካን ወዳጆቿን እያስተባበረች ያለችበት ሁኔታ ላይ የክትባቱ መገኘት ለደ/ር ቴዎድሮስ ጥሩ እድል ይከፈታል የሚል ግምት ቢሰጥም መድሃኒቱ ተገኘም አልተገኘ ቴዎድሮስ አድሃኖም ለጤና ተቋሙ ከፍተኛ ለጋሽ ከሆነችው አሜሪካ ጋር ያላቸው ተቀባይነት ሙሉ በሙሉ በማክተሙ እድል ሊሆን አይችልም የሚሉ ትንተናዎችም ተሰጥቷል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመጥፎነቱ የሚታወቀው እና በአሜሪካ መንግስት ሽብርተኝነትን መዝገብ ላይ እስከአሁን ያልተፋቀው ህወሓት አባል እና ከፍተኛ አመራር እንደነበሩ ይታወቃል።

LEAVE A REPLY