ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ሱዳን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ አሞላልን በተመለከተ ከኢትዮጵያ የቀረበላትን ሃሳብ አልቀበልም በማለት ማፈንገጧና ዳግም ከግብፅ ጋር መቆሟ ታወቀ።
በአባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ እየገነባቸው ባለው አወዛጋቢ ግዙፍ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን የስምምነት ሐሳብ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አልቀበልም ማለታቸው ተሰምቷል: :ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሐሳብ ውድቅ ያደረጉት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለው ግድብን በተመለከተ ያልተፈቱ ቴክኒካዊና ሕጋዊ ጉዳዮች አሉ ከሚል እሳቤ እንደህነም ተነግሯልል። ግብጽና ሱዳን በምዕራብ ኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው ታላቁ የህዳሴ ግድበን ከወንዙ የምናገኘውን የውሃ መጠን በከፍተኛ መጠን ይቀንስብናል የሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው::
ሦስቱ አገራት ከወራት በፊት በአሜሪካና በዓለም ባንክ አማካይነት ዋሽንግተን ውስጥ በከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው አማካይነት ተከታታይ ድርድሮች ቢያደርጉም ከመቋጫ ላይ መድረስ ሳይችሉ ቀርተዋል። በተለይ ኢትዮጵያ በመጨረሻ ላይ የቀረበው የስምምነት ሰነድ ጥቅሟን የሚነካና ለግብጽ ያደላ ነው በሚል እራሷን ከፊርማው ማራቋ አይዘነጋም።
ለበርካታ ዓመታት የወንዙን ከፍተኛ መጠን ውሃ በመጠቀም የምትታወቀው ግብጽ፤ የግድቡ ግንባታና ውሃ አሞላልን በተመለከተ ከፍያለ ስጋት ስላደረባት፣ አሜሪካንን ጨምሮ የአረብ አገራትን ድጋፍ ለማሰባሰብ ባለፉት ወራት ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። በዚህ መሠረት የአረብ ሊግ አገራትም የግብጽን ፍላጎት የሚያስከብር የአቋም መግለጫ ሲያወጡሱዳን መግለጫውን ተቃውማ፣ ከጉዳይ እራሷን ማግለሏን ገልጻ ነበር። በዚህ አቋሟ ከኢትዮጵያ ምስጋና፣ ከግብፅ ጠንከር ያለ ወቀሳን በጊዜው አስተናግዳለች ።