በሰዐት 30 ሺኅ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግድ ተርሚናል መገናኛ አካባቢ ይገነባል ተባለ

በሰዐት 30 ሺኅ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግድ ተርሚናል መገናኛ አካባቢ ይገነባል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በአዲስ አበባ ፣ መገናኛ አካባቢ ዘመናዊ የሆነ የብዙኃን ትራንስፖርት ተርሚናል ግንባታ በቅርቡ ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ  የተለያዮ የልማት ሥራዎችን እያካሄደ የሚገኘው ከተማ መስተዳደሩ፤ በሰዐት እስከ 30 ሺኅ ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግደው  አዲስ ተርሚናል ከቀላል ባቡር አገልግሎትና ከፈጣን አውቶብስ አገልግሎት ጋር የተሳሰረ እንደሚሆን ይፋ አድርጓል።

የብዙኃን ትራንስፖርት ተርሚናሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያና የመንገደኞች መተላለፊያ ድልድይ ፣ እንዲሁም ባለ ስምንት ወለል ህንፃን ያካትታል ተብሎለታል:: ግንባታው ሲጠናቀቅና ወደ ሥራ ሲገባ በአካባቢው የሚታየውን መጨናነቅ ከመቀነሱ ባሻገር ፣ የሕዝብ ትራንስፖርትን በማዘመን በኩል የጎላ ድርሻ እንደሚኖረው ከወዲሁ ተተንብዮለታል።

LEAVE A REPLY