ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የሱዳን ጦር በምዕራብ አርማጭሆ ኮረደም፣ ልዩ ስሙ “አሴራ” በተባለ አካባቢ ትናንት ግንቦት 5/2012 ዓ.ም በአማራ ልዩ ኃይልና በሚሊሻዎች፣ እንዲሁም በገበሬዎች ላይ ተኩስ እንደተከፈተ ተነገረ።
ትናንት ማለዳ 12 ሰዐት ላይ የሱዳን ጦር በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ተኩስ መክፈቱን በስፍራው ያሉ ታማኝ ነዋሪዎችን ጠቅሶ የዘገበው አስራት ሚዲያ ነው።
አስራት ሚዲያ ጉዳዩን ለማጣራት የደወልንላቸው የምዕራብ አርማጭሆ የብልጽግና ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ አንዷለም ስንሻው ግጭት መፈጠሩን መረጃ እንደደረሳቸው አምነው ፤ በጉዳዮ ላይ የተጣራ መረጃ ስለሌላቸው ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ ገልጸውልኛል ብሏል።
የሱዳን ጦር ከመጋቢት 25/2012 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ተዳፍሮ ይገኛል በማለት አስራት ቴሌቪዥን በተደጋጋሚ ሲዘግብ ነበር ። ጦሩ በሰፈረባቸው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች ላይ የሚያለሙ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ጦሩ መሬታቸውን ለቆ እንዲዲወጣ ሲወተውቱ መሰንበታቸውም ይታወሳል።