በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿ በሙሉ ያገገሙላት ኤርትራ፤ ከነገ ጀምሮ ሠፊ ምርመራ ልታደርግ ነው

በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿ በሙሉ ያገገሙላት ኤርትራ፤ ከነገ ጀምሮ ሠፊ ምርመራ ልታደርግ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በሀገሪቱ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ተከትሎ ኤርትራ ከነገ ግንቦት 9/2012 ዓ/ም ጀምሮ ሠፊ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ እንደምትጀምር ገለፀች።

የኢሳይያስ አፈወርቂ መንግሥት የሚያከናውነው የጤና ዘመቻና ምርመራ በቅድሚያ በአስመራ ከተማ የሚጀመር ሲሆን በቀጣይ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የሰዎች ዝውውር ይካሄድበታል ተብለው በተገመቱ የሀገሪቱ የድንበር ከተሞች፣ እንዲሁም በተለያዮ መንደሮች ላይ ይደረጋል ነው የተባለው።

በኤርትራ በቫይረሱ ተይዘው የነበሩ ሁሉም ሰዎች ቢያገግሙም፤ ቫይረሱ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ማለት ስላልሆነ አሁንም ህዝቡ ጥንቃቄ እንዳይለየው የሀገሪቱ መንግሥት በተደጋጋሚ በማሳሰብ ላይ ይገኛል።

የኮቪድ 19 ቫይረስ በመላ ሀገሪቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ እስኪረጋገጥ ድረስ ዜጎች መንግሥት ያወጣውን ሕግ እንዲያከብሩም የየኢሳይያስ አፈወርቂ መንግሥት ቆምጨጭ ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

LEAVE A REPLY