ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት በተደረገ 4.044 (አራት ሺኅ ዐርባ ዐራት) የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ 19 ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 306 መድረሱን ጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።
በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ የኮቪድ 19 ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው ። 15 ወንድ እና 4ሴት የቫይረሱ አዲስ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ያመላከቸው መግለጫ ፤ እድሜያቸው ከ16-55 መሆኑን አረጋግጧል::
በተሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ መሠረት የታማሚዎች ሁኔታ :-
1. የውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው 15 ሰዎች
2. ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው 2 ሰዎች
3.የ ውጪ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው 2 ሰው ሆኖ ተመዝግቧል።
የታማሚዎች መኖሪያ አድራሻ:-️
-2 ሰዎች- ከአዲስ አበባ
-2ሰዎች- ከትግራይ ሴቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ
-11ሰዎች- ከሱማሌ ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ
-2ሰዎች – ከኦሮሚያ ክልል (ጊንጪ ከተማ በቤት ለቤት አሰሳ እና ቅኝት የተለየ)
-1 ሰው – አማራ ክልል መተማ ለይቶ ማቆያ መሆናቸውን ጤና ሚኒስትር በመግለጫው ላይ አስፍሯል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው (ከኦሮሚያ) ከኮሮና ቫይረስ ያገገመ ሲሆን፣ እስከ አሁን በአገሪቱ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 113 መድረሱ
ተነግሯል፡፡️