ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በእስራኤል የቻይና አምባሳደር በቴል አቪቭ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸውን የተለያዮ ዓለም ዐቀፍ ሚዲያዎች በመዘገብ ላይ ናቸው።
አምባሳደር ዱ ዌ አልጋቸው ላይ ሕይወታቸው አልፎ የተገኘ ሲሆን ለሞታቸው ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የተገለፀ ነገር አለመኖሩ ደግሞ የ58 ዓመቱን አምባሳደር አሟሟት አነጋጋሪ አድርጎታል።
በየካቲት ወር ላይ በእስራኤል – ቴልአቪቭ የቻይና አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደሩ ከዚህ በፊት ዩክሬን ውስጥ የቻይና ልኡክ ሆነው ሠርተዋል::
አምባሳደሩ የአንድ ልጅ አባት ሲሆኑ ባለቤታቸውም ሆነ ልጃቸው አደጋው ሲደርስ በአገር ውስጥ እንዳልነበሩ ተገልጿል።