ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት 24 ሰዐት ውስጥ ለ4.225 (ለአራት ሺኅ ሁለት መቶ ሀያ አምስት) ሰዎች የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር አስታወቀ፡፡
ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ አምስቱ ወንዶች ፣ ሥድስቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው። አራት ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ ስድስት ሰዎች ከሱማሌ ክልል(ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ)፣ እንዲሁም አንድ ሰው ከአማራ ክልል (ሰሜን ሸዋ ዞን፣አጣየ ከተማ ለይቶ ማቆያ) እንደሆነ መግለጫው ያሳያል።
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም በኮቪድ 19 ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ መንግሥት ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል ። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 317 ደርሷል።