ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም በዓለም ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች እየተፈተኑ ነው

ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም በዓለም ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች እየተፈተኑ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሁሉም ሀገራት የጤና ባለሥልጣናት፣ ዓለም ኮሮናቫይረስን በተመለከተ እስካሁን የተወሰደው እርምጃ ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ ሊያቀርቡ ይችላሉ ተባለ።

የዓለም ጤና ድርጅት 194 አባል አገራት ተወካዮች የኮሮናቫይረስ ወረርሸኝን ዋነኛ አጀንዳ በማድረግ በኢንተርኔት አማካይነት 73ኛ ጉባዔያቸውን ያካሂዳሉ። በጉባዔው ላይ በመላው ዓለም ከ300 ሺኅ በላይ ሰዎችን በቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዙሪያ የዓለም ጤና ድርጅትና አባል አገራቱ የወሰዱት እርምጃ ላይ ጥያቄዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአውሮፓ  ኅብረት ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ከአውስትራሊያና ኒው ዚላንድ ጋር በመሆን ዓለም ዐቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ስለተወሰዱ እርምጃዎች ምርመራ እንዲደረግ፣ ብሎም ከዚህ በሽታ ምን ትምህርት እንደሚወሰድ የሚነሳውን ጥያቄ በመሪነት እንደሚያቀርብ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

የሕብረቱ ቃል አቀባይ በሚደረገው ግምገማ ላይ መመለስ ያለባቸው በርካታ ጥያቄዎች እንዳሉ አስታውሰው፤ “አንዱ አንዱን ለመወንጀል ጊዜው አይደለም” በማለት የአሜሪካና የቻይናን ውዝግብ አጣጥለዋል።

በዚህ ጉባዔ የዓለም ጤና ድርጅት ወረርሽኙን በተመለከተ በወሰዳቸው እርምጃዎች ሳቢያ በርካታ ጥያቄዎች እንደሚነሱበት በመነገር ላይ ነው።  ይህንን አስመልክቶ የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ዶክተር ማርጋሬት ሃሪስ”ይህ ጉባዔ ሁልጊዜም በርካታ ጥያቄዎች ለድርጅቱ የሚቀርብበት ነው፤ የዘንድሮው አዲስ ነገር ሊሆን እንደማይችል እገምታለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ቃል አቀባዮ ይህን ይበሉ እንጂ ከኮሮና ቫይረስ መስፋፋትና ከፍተኛ ጉዳት አኳያ በመጥፋቱ የሚታወቀው የህወሓት ፓርቲ አባል የነበሩት ዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ከዛሬ (ሰኞ) ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የቪዲዮ ኮንፈረንስ ጉባዔ በዓለም ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች ከባድ ፈተና እንደሚጠብቃቸው ተመልክቷል።

LEAVE A REPLY