ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንኮች የሚወጣ የገንዘብ መጠን ላይ ገደብ የጣለ አዲስ መመሪያ አወጣ።
መመሪያው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም የባንኩ ዋና ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ አድርገዋል።
በተጣለው እገዳ መሠረት ለግለሰብ በቀን 200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺኅ ብር)፣ በወር ደግሞ 1.000.000 (አንድሚሊየን ብር) ነው ያሉት የብሔራዊ ባንክ ገዢ፤ ለኩባንያዎች ደግሞ በቀን እስከ 300,00 (ሦስት መቶ ሺኅ) ብር እና በወር እስከ 2.500 (ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን) ብር ድረስ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል::
ብሔራዊ ባንኩ ይህን የገንዘብ ገደብ የጣለው ህገወጥ ገንዘብ ዝውውርን ለመግታት እንደህነ ያስታወሱት ዶክተር ይናገር ደሴ፤ “የእዚህ መመርያ ተግባራዊ መሆን የሚያሳስበው ህጋዊ ያልሆነ ሰው ነው” ብለዋል።
የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ፤ በልዩ ልዩ ሁኔታ የገንዘብ ገደቡ የማይመለከታቸው ደንበኞች በመመርያው መካተቱንናይህም ለሁሉም ባንክ ፕሬዝዳንቶች ሥልጣን የሰጠ ቢሆንም፤ ብሔራዊ ባንኩ ይህንኑ አሠራር በቅርበት ይከታተለዋል ሲሉም ገልጸዋል።
ባንኮችም ይህንኑ መመርያ በተፈቀደው መንገድ ብቻ እንዲያደርጉ መመርያው እንደሚያስገድዳቸው የጠቆሙት ዋናው ገዥ፤ መመርያውን እና የገንዘብ ገደቡን የተላለፉ ባንኮች ለከፈሉት ክፍያ 25 በመቶ የገንዘብ ቅጣት እንደሚቀጡም ከወዲሁ አስጠንቅቀዋል።