ዶ/ር አብርሃም በላይ ከክልሎች እና የተቃዋሚዎች ጋር ጦርነት የመጨረሻ አማራጭ ነው አሉ

ዶ/ር አብርሃም በላይ ከክልሎች እና የተቃዋሚዎች ጋር ጦርነት የመጨረሻ አማራጭ ነው አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና “ጦርነት የመጨረሻ የመፍትኄ አማራጭ እንጂ፣ ተፈላጊ አማራጭ አይደለም” ሲሉ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  ዶ/ር አብረሃም በላይ አስታወቁ።

ሰሞነኛው የህወሓትና የተለያዮ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴን አስመልክተው ዶክተር አብርሃም በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ “ሰላምን አብዝቶ መፈለግ ፍርኃትን ሣይሆን የመሪዎች ጥበብን እና ለሰው ልጆች ያለን ክብር ያሳያል” ብለዋል፡፡

“የሌላውን ባናውቅም የእኛ መንግሥት ጦርነት እና ድህነት ለህዝባችን አይገባም ብሎ በማመኑ፣ ሕዝባችንን ወደ ልማትና ብልፅግና ማሻገር ጊዜው አሁን ነው ብሎ እየሠራ ይገኛል” ያሉት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም  መንግሥት በተጠላለፉ ፈተናዎች ውስጥ ሆኖ ያለ እረፍት ኢትዮጵያን ወደ ተሟላ ሰላም፣ ልማትና ብልፅግና ለማሸጋገር ቅድሚያ ሰጥቶ እየሠራ ነው ሲሉ የብልፅግናን ወቅታዊ አቋም አመላክተዋል።

“ለኢትዮጵያ ጦርነት ከሚመኙት አካላት ጋር መንግሥት ውይይት እና ምክክር ማድረግ የሚመርጠውም ይህንን የብልፅግና ጉዞ ለአፍታም ቢሆን እንዲደናቀፍ ስለማይፈልግ እና ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ ስለሚያምን ነው” በማለት በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል።

የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ፤ ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም፣ ተገዶ ካልተገባ በስተቀር፣ ከሰው ህይወት ማጣት በላይ የሚያከስርና የሚጎዳ ምንም ነገር የለም በማለት ግጭት ለመፍጠር ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ምክር ለግሰዋል።

LEAVE A REPLY