ዶክተር ሊያ ታደሰ  የኮሮና ታማሚዎች ቁጥር ስህተት መኖሩን ገለፁ

ዶክተር ሊያ ታደሰ  የኮሮና ታማሚዎች ቁጥር ስህተት መኖሩን ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ3.271 (ለሦስት ሺኅ ሁለት መቶ ሠባ አንድ) ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 14 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ፡፡

ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት በሚታይባት ኢትዮጵያ በተለይም ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተከበረውን የፋሲካ በዓልን ተከትሎ በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍሎችና በአዲስ አበባ ልቅ የሆነ የሰዎች ንክኪ መከሰቱን ተከትሎ በቀጣይ በየቀኑ የሚመዘገቡ አዳዲስ  በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ እየተባለ ይገኛል ።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 11 ወንድ እና 3 ሴቶች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፤ እድሜያቸውም ከ9 እስከ 68 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ተከትሎ ፤ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 365 አድርስታል፡፡

በትናንትናው እለት 4 ሰዎች ከቫይረሱ በማገገማቸው በአጠቃላይ በሀገራችን ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 120 መድረሱን የጠቆመው የጤና ሚኒስትሯ መግለጫ፤  ከዚህም በተጨማሪ ትናንት ቫይረሱ በምርመራ ተገኘባቸው ከተባሉት 35 ሰዎች ውስጥ  አንድ ግለሰብ ቀደም ሲል (ግንቦት 9 ) በወጣው መግለጫ ሪፖርት ተደርጎ የነበረና በድጋሚ በትናንትናው መግለጫ የተካተተ መሆኑን ያሳያል።

ይህ ከአጣዬ ለይቶ ማቆያ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ታማሚ የትናንቱ ሪፖርት ውስጥ በመካተቱ የቁጥር ስህተት መፈጠሩን ያመኑት ዶክተር ሊያ ታደሰ ትናንት በቫይረሱ የተያዙት 34 ሰዎች ናቸው በሚል እንዲስተካከል ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY