ለድርድር የሚቀርብ ሀገራዊ ጉዳይ የለም ሲል፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ማኅበር አሳሰበ

ለድርድር የሚቀርብ ሀገራዊ ጉዳይ የለም ሲል፣ የቀድሞ ሠራዊት አባላት ማኅበር አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ታላቁ የህዳሴው ግድብን አስመልክቶ ለድርድር የሚቀርብ ሃገራዊ ጉዳይ በምንም መልኩ ሊኖረን አይችልም ሲሉ የቀድሞ ምድር ጦር ሰራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች ማህበር አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በሚዳፈር እና ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚጻረር የጎረቤት አገራት ተግባር ማዘኑን ባወጣው መግለጫ የጠቆመው ማኅበሩ ፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ አፍራሽ ተልዕኮን ባነገቡ የውጭና የውስጥ ኃይሎች ላይ ያለውን አቋም  ተንተርሶ በባለ ሦስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቻለሁ ብሏል፡፡

የቀድሞ ምድር ጦር ሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞችበአቋም  መግለጫው :- “ማህበሩ ሱዳን የያዘችውን አሁናዊ አቋም፣ ግብጽ የህዳሴው ግድብ መሰረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ የምታራምደውን ግድቡን የማስተጓጎል እና የጠብ አጫሪነት ተግባር ፣ እንዲሁም ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር  ግንኙነት በማድረግ አፍራሽ ድርጊትን ለመፈጸም ሴራን የሚሸርቡ የውስጥ አርበኞችን ተግባር አውግዛለሁ” ሲል አስታውቋል፡፡

እነዚህን ታሪካዊ ጠላቶቻችንን ከማውገዝ ባሻገር፤ እንደየ አመጣጣቸው ለመመከት መንግሥት በሚወስደው ማንኛውም ዓይነት አጸፋዊ እርምጃ ሁሉ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ  ከጎኑ ለመሰለፍ አቋም ይዣለሁ ሲል ማኅበሩ ይፋ አድርጓል ።

LEAVE A REPLY