መንግሥት ከደምቢ-ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ሊከሰስ ነው

መንግሥት ከደምቢ-ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ ሊከሰስ ነው

Federal Democratic Republic of Ethiopia - vector map

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በፀጥታ ስጋት ወደ ትውልድ ስፍራቸው ሲመለሱ ባልታወቁ ሰዎች ከታገቱ 6 ወር ሊሞላቸው ጥቂት ቀናት በቀሩት የደምቢዶሎ ዮንቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ መንግሥት ሊከሰስ ነው ተባለ።

እስካሁን ድረስ ተማሪዎቹ ስላሉበት ጉዳይ የሚያውቅ አካል አለመኖሩ፣ እንዲሁም መንግሥት በጉዳዩ ላይ የሰጣቸው መግለጫዎች  እና በጥቅሉ ለጉዳዩ የሰጠው ትኩረት አነስተኛ   ነው የሚል ወቀሳ ከብዙኃኑ ሕዝብ መሰማቱን ተከትሎ በመንግሥት ላይ ክስ ለመመስረት መነሻ ምክንያት ሆኗል መባሉን ሰምተናል ።

መንግሥት በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ በቂ መረጃ እየሰጠን አይደለም ያለው የኢትዮጵያ ህግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር የማህበር ሥራ አስፈፃሚ ሌንሳ ቢየናም፤ መንግሥት ጉዳዩ ስለመከሰቱ በይፋ ካመነ ወዲህ የተማሪዎቹን ወላጆች ከማነጋገር ጀምሮ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ጀምረን ነበር ካሉ በኋላ፤ “ጉዳዮ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላትን ደጋግመን የተደረሰበትን ውጤት ብንጠይቅም፤ ይሄ ነው የሚል ምላሸ ማግኘት ግን አልቻልንም። በመሀል ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት ወደኋላ ጎትቶናል” ሲሉ ተናግረዋል።

“በወቅቱ የተማሪዎቹ ወላጆች ልጆቻቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ሲነግሩን በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ሳይቀር ጫና ለመፍጠር የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ጀምረን የነበረ ቢሆንም፤ ይወጡ የነበሩ መረጃዎች ግልፅ አለመሆናቸው እንደ ማኅበር ብዙ እንዳንጓዝ እንቅፋት ከሆኑብን ምክንያች መካከል ተጠቃሹ ነው” ያሉት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ “መንግሥት የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ ስላለበት በቂ ምላሽ፣ እንዲሁም መፍትኄ ሊሰጥ ይገባል” ብለዋል ።

ሆኖም አሁን በሥልጣን ላይ ያለው የዶክተር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ይህንን የማያደርግ ከሆነ ግን፣ ጉዳዩ በሀገርም ሆነ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኝ ጫና እናደርጋለን  የሚሉት የማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ ጫናውመንግሥትን እስከ መክሰስ ይደርሳል ሲሉም አስጠንቅቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY