በአዲስ አበባ  ዓለም ዐቀፍ መስጂድ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

በአዲስ አበባ  ዓለም ዐቀፍ መስጂድ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በአዲስ አበባ ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የመስጂድ ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል የመሠረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀመጠ ።

የመዲናዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር እድሪስ እና የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሡልጣን አማን  የመሰረት ድንጋዮን አስቀምጠዋል፡፡

ዓለም ዐቀፍ መስጂድ ግንባታው መሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማው ለሚገኙ 71 መስጂዶች የይዞታ ሰነድ ማረጋገጫ አስረክበዋል፡፡

ከግዙፉ አፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ፊት ለፊት በሚገኝ 30 ሺኅካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚገነባው  መስጂድ በውስጡ እስላማዊ ማዕከል እንደሚታነጽበት እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

“የሰው ልጅ የሚያስከብረው መልካም ሥራው በመሆኑ ይህን አስተዋጽዖ ላደረጉት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ እና ኢ/ር ታከለ ኡማ ምስጋና ይገባል” ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ እንድሪስz፤ የመስጂዱ ግንባታ የሙስሊሙ ማኀበረሰብ የረጅም ዓመታት ጥያቄን የሚመልስ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY