ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአስቸኳይ አዋጁን ጥሰው፤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ተሰብስበው ጫት ሲቅሙ የተገኙ 36 ግለሰቦች ተቀጡ።
ግለሰቦቹ እያንዳንዳቸው 20 ሺኅ ብር እና በእስራት መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት፤ ሀያ አንድ ተከሳሾችን እያንዳንዳቸው በ20 ሺኅ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
የተላለፈውን የገንዘብ ቅጣት (ሀያ ሺኅ ብሩን) መክፈል ያልቻሉ አስራ አምስት ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ15 ቀን እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ እንዳስተላለፈባቸው ታውቋል።