ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሀገረ እስራኤል 35ኛው ጠቅላይ ሚኒስትር እና ሚኒስትሮች ቃለ መሐላ መፈጸማቸውን ተከትሎ 119 ቤተ እስራኤላውያን ዛሬ ወደ ሀገራቸው ይገባሉ።
በኢትዮጵያ የቤተ እስራኤላውያን ማኅበርም ቤተ እስራኤልያውያኑ ዛሬ ሀገራቸው እንደሚገቡም ማረጋገጫ የሰጡ ሲሆን የሀገሪቱ ዜና አውታሮችም ጉዞውን በተመለከተ እየዘገቡ ናቸው፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተቀሰቀሰ በኋላ ቤተ እስራኤላውያኑ ዛሬ ወደ ሀገራቸው እስራኤል ሲገቡ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑም ተነግሯል።
ቤተ እስራኤላውያኑ ዛሬ ከሰዐት በኋላ ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ እስራኤል በረራ ያደረጉ መሆናቸውም ተረጋግጧል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በእስራኤል በአዲስ ካቢኔ ከተሾሙት ሚኒስትሮች መካከል ሁለቱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው አይዘነጋም፡፡