የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን በማጥበቅ ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል አለብን || ጠቅላይ...

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን በማጥበቅ ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል አለብን || ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭት አኳያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈፃፀም ማጥበቅና ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀምን በማጥበቅ ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ ማሻሻል አለብን ።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤአፈፃፀም በተመለከተ እንደገለጹት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ከጊዜ ወደጊዜ ወጥነት ባለው መልኩ እየተሻሻለ ኮሮናቫይረስን እንዳይስፋፋ የራሱን ሚና እየተጫወተ ነው።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየታየ በመሆኑና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ዜጎች ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑ የተሰጠውን ትኩረት ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የሚያመላክት መሆኑን ተናግረዋል።

“በመሆኑም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያወጣቸውን ዝርዝር ደንቦች በትክክል እንዲተገበሩ በጥብቅ መከታተል ያስፈልጋል” ብለዋል።

“በተለይ በትራንስፖርትና ሌሎች ዘርፎች ላይ የአዋጁን ደንቦች በሚገባ ለማስፈፀም እንዲያስችል ለተጠያቂነት በሚያመች መልኩ አዋጁን ማየት እንዳለብን ተመልክተናል” ሲሉ ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል።

“አዋጁን በትክክል ተረድቶ ከመፈፀምም ይሁን ከማስፈፀም ስህተቶች ሊገጥሙ ይችላሉ” ያሉት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጓ፤ የአዋጁ አስፈፃሚዎች የሚያደርጉት ክልከላዎች የዜጎችን ህይወት ለማዳን እንደሆነ በመገንዘብ ደንቦቹን መተግበር ከሁሉም እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

በተለይም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ከማድረግና ካለማድረግ ጋር ሰዎች ያለ አግባብ ይታሰራሉ ከሚለው ቅሬታ ጋር አያይዘውም “ህዝቡ ሰዎች በሚበዛባቸው ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በማናቸውም ቦታዎች ማስክ ቢያደርግ ይጠቀም እንደሆን እንጂ አይጎዳም” ሲሉ መክረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስከበር ሽፋን ውስጥ የሙስና ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ መንግስት እንዴት ይከላከላል? ለሚለው ጥያቄም “ህዝቡ ህይወቱን አስይዞ መደራደር የለበትም” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ግን ወደ አላስፈላጊ ድርድር የሚገባ ህግ አስከባሪ ካለ ጥቆማ በመስጠት የዜጎችን ህይወትና የሙስና ወንጀልንም ከመንግስት ጎን ሆኖ እንዲከላከል ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ ፡ – የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ

LEAVE A REPLY