ሕዝብ በኮሮና ፍራቻ ለመደበኛ ሕክምና ሆስፒታል መሄድ አቁሟል ተባለ

ሕዝብ በኮሮና ፍራቻ ለመደበኛ ሕክምና ሆስፒታል መሄድ አቁሟል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኅብረተሰቡ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ወደ ሕክምና ተቋማት መሄድ ማቆሙን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

እንደ ተቋሙ መግለጫ ከሆነ እናቶችና የሕጻናት ጤና አገልግሎትን ጨምሮ በመደበኛ የሕክምና አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት እየታየ ነው።
በጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ የተመራ ቡድን በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የአሰላ ሪፌራል ሆስፒታል የመደበኛ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ሁኔታ የጎበኘ ሲሆን ፤ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በተፈጠረ ስጋት በሀገር ደረጃ የእናቶችና ህፃናት ጤና አጠባበቅን ጨምሮ ለመደበኛ የህክምና አገልግሎት የሚሰጠው ትኩረት ቀንሷል መቀነሱን መታዘባቸውን ሓላፊው ገልጸዋል።
የእናቶችና ህፃናት ጤናን ጨምሮ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ መንግስት በአዲስ መልክ ስትራቴጂ በመንደፍ እየሰራ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY