በኃየሎም አርአያ የበርሃ ስም የሚጠራው “ፈንቅል” የትግራይ ወጣቶች አመጽ አክሱም ደረሰ

በኃየሎም አርአያ የበርሃ ስም የሚጠራው “ፈንቅል” የትግራይ ወጣቶች አመጽ አክሱም ደረሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከቀናት በፊት የተጀመረው የትግራይ ወጣቶች ተቃውሞ ወደ ትግራይ ሕዝባዊ አመጽ ብዙኃኑን የኅብረተሰብ ክፍል እያካተተ መምጣቱን ታማኝ ምንጮች ከመቀሌ አድርሰውናል።

ለይስሙላ በደብረፂዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው፣ በስውር በአቦይ ስብሐት ነጋ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ አባይ ፀሐዬ እና ስዮም መስፍንን በመሳሰሉ ነባር የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ ሹማምንት የሚመራው ህወሓት በዚህ ወቅት አመራሮቹን በመቀሌ፣  አክሱም ሆቴልና የተመረጡ ሥፍራዎች ታማኝ ወታደሮቹ እያስጠበቀ ይገኛል።
ከላይ የተጠቀሱትን እና ሙስናና ሰብኣዊ ጥሰቶችን ጨምሮ በበርካታ ከባድ ወንጀሎች የሚፈለጉት የድርጅቱ ነባር ታጋዮች የትግራይ ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ በስርዓቱ ላይ ተቃውሞውን በግልፅ እያሰማ መሆኑን ተከትሎ ከፌደራል መንግሥቱም ሆነ ከክልሉ ነዋሪ ሊደርስባቸው የሚችለውን እርምጃ በመፍራት ከትናንት ምሽት ጀምሮ አንዳንዶች ለሁለት ዓመታት የተቀመጡበትን ሆቴል ለቀው በመውጣት በመቀሌ ውስጥ ባስቀመጧቸው ደጋፊዎቻቸው መኖሪያ ቤት መጠለል እንደጀመሩም ሰምተናል።
ወደ ተለያዮ የትግራይ ከተሞች የተዛመተውና ዛሬ ሠባተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የትግራይ ወጣቶች አመጽ ወደ አክሱም ከተማ በመሻገር የተቃውሞ አድማሱን አስፍቷል ነው የተባለው። በከተማዋ ያረጀው ህወሓት የትግራይ ሕዝብን መምራትም ሆነ ማስተዳደር አይችልም ያሉ ሰልፈኞቹን ለመበተን ከመጣው የክልሉ ልዮ ኃይል ጋር ከፍተኛ ግጭት ውስጥ ገብቷል።
በአመጹ ነዋሪዎች የህወሓት ንብረት የሆኑ ሁለት መኪኖችን በእሳት የጋዮ ሲሆን፣ በተሳሳተ ፕሮፐጋንዳ የህወሓት ደጋፊ በመሆን በዝምታ የተዋጠውን ቀሪውን የኅብረተሰብ ክፍል “ተነስ” በማለት ማነቃቃታቸው ታውቋ።
በትግራይ ሕዝብ ዘንድ በእጅጉ የሚወደደውና በህይወት በሌለው ጀነራል ኃየሎም አርአያ የጦር ሜዳ ሁለተኛ ስም የተሰየመው “ፈንቅል” የትግራይ ወጣቶች ተጋድሎ ህወሓት እስኪወገድና የድርጅቱ መሪዎች በሕግ እስኪጠየቁ ድረስ አመጹ እንደሚቀጥል የወጣቶቹ አደረጃጀት በማኅበራዊ ድህረ ገፆች መልእክት አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY