ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ኢንቨስተሮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት የተቋቋመው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና በጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር አምባሰደር ግርማ ብሩ የሚመራው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ሲያካሂድ፤ በስብሰባው የውጭ ባለሀብቶች በአገራችን እያደረጉ ባለው የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴ እያገጠሙ ያሉ ችግሮች ምንድን ናቸው በሚለው ላይ በጥልቀት መክሯል።
በመድረኩ በቀጣይ መሠራት በሚገባቸው ሥራዎች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት፤ የቅንጅት መድረኩ ታህሳስ 23/ 2012 ዓም ባደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ፣ ከዚህ በፊት የነበረውን የቅንጅት መድረክ እንደገና ለማስጀመር እና የውጭ ባለሀብቶችን ችግር በቅርበት በመከታተል መፍትኄ ለማፈላለግ እንዲቻል ዳግም እንዲቋቋም መደረጉ አይዘነጋም።