ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኮሮና ቫይረስ የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች!
በኮቪድ 19 ቫይረስ መያዟን ተከትሎ በየካ ኮተቤ ሆስፒታል ተኝታ የነበረች ኢትዮጵያዊት ነፍሰ ጡር ልጇን በሰላም መገላገሏ ነው የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያስታወቀው።
የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ “በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ ልጇን በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላግላላች። ህፃኑና እናትየው በዚህ ወቅት በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ” ሲሉም ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ማገገሚያነት እያገለገለ ባለው በየካ ኮተቤ ሆስፒታል ዛሬ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እመጫቷን ከመጠየቃቸው ባሻገር የተለያዩ ስጦታዎችን አበርክተውላታል።