ከንቲባ ታከለ ኡማ ዒድን ከሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ተፈናቃይ ሙስሊሞች ጋር አከበሩ

ከንቲባ ታከለ ኡማ ዒድን ከሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ተፈናቃይ ሙስሊሞች ጋር አከበሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ችግር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ከሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የዒድ አልፈጥር በዓልን ማክበራቸው ተሰማ።

ኢንጂነር ታከለ በዓሉንና ውሎአቸውን በተመለከተ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የዒድ አልፈጥር በዓልን በሱማሌ እና ኦሮማያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው ችግር ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ እህትና ወንድሞች ጋር በጥሩ ሁኔታ አክብረናል” ብለዋል።
በዋና መዲናዋ የተለያዮ ኅብረተሰባዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ሥራዎችን በመሥራት የሚታወቁት ከንቲባ ታከለ ኡማ ለረመዳን ፆም ፍቺ  ከባለሃብቶች ያሰቧሰቧቸውን ለምግብ የሚውሉ እና የንጽሕና መጠበቂያ የተለያዩ ስጦታዎችን ለተፈናቃዮቹ ሙስሊሞች አበርክተዋል።

LEAVE A REPLY