በአማራ ክልል 1 ሺኅ ጋብቻዎች ተቋረጠ፤ ያለአቻ ገብቻ ተበራክቷል

በአማራ ክልል 1 ሺኅ ጋብቻዎች ተቋረጠ፤ ያለአቻ ገብቻ ተበራክቷል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአማራ ክልል በተለያዮ ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጣስ ሊከናወኑ የነበሩ ብዛት ያላቸው ያለ ዕድሜ ጋብቻና ሠርጎችን እንዲቋረጡ ማድረጉን የክሌሉ መንግሥት አስታወቀ።

በአማራ ክልል ሕግን በመተላለፍ ሊፈጸሙ የነበሩ ከ 1 ሺህ በላይ ያለዕድሜ ጋብቻዎች እንዲቋረጡ መደረጉን የጠቆመው የክልሉ ሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፤ ያለ አቻ ጋብቻዎቹ በከፍተኛ ሁኔታ የጨመሩት ከኮሮና ቫይረስ መስፋፋት በኋላ ነው ብሏል።
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የትምህርት ቤቶች መዘጋትን ወላጆች እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በቀደመ ጎጂ ባህል መሠረት ለአቅመ ትዳር ያልደረሱ ታዳጊ ሴቶችን በዕድሜ በብዙ ዓመት ለሚበልጧቸው ሰዎች ሊድሯቸው ሲጣደፉና ድግስ ሲደግሱ ደርሼባቸዋለሁ ያለው ተቋም ቁጥራቸው ከአንድ ሺኅ በላይ የሚሆኑ ያለ ዕድሜ ጋብቻዎችን እውን ሳይሆኑ እንዲቋረጡ አድርጊያለሁ ሲል ገልጿል።
በሌላ በኩል ማስቆም ያልተቻለና አሁንም ጉዳዮቹ በሕግ አግባብ እየታየ  585 ያለዕድሜ ጋብቻዎች መፈጸማቸውን የክልሉ ሴቶች እና ሕፃናት ቢሮ አጋልጧል።

LEAVE A REPLY