በአ/አ በአንድ ግለሰብ የተያዘ 460 ሺኅ ካሬ ሜትር መሬት ለአርሶ አደሮች ተከፋፈለ

በአ/አ በአንድ ግለሰብ የተያዘ 460 ሺኅ ካሬ ሜትር መሬት ለአርሶ አደሮች ተከፋፈለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዞ የነበረ 460 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ለተለያዮ አርሶ አደሮች እንዲከፋፈል መደረጉ ተገለጸ።

ከንቲባ ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝና በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ግለሰብ ተይዞ የነበረ 460 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ለአርሶ አደሮች እንዲተላለፍ አድርገዋል ነው የተባለው።
ከፍተኛ የሆነ የመሬት እጥረት ባለባት ከተማ ይህን ያህል ሰፊ መሬት በአንድ ግለሰብ ተይዞ መቀመጡ እያነጋገረ ነው።ከግለሰቡ ላይ የተነጠቀው መሬት ከ60 በላይ ለሚሆኑ ነባር አርሶ አደሮች የተላለፈው የከተማ ግብርና ልማት እንዲያካሂዱበት እንደሆነ ነው የተገለጸው።

LEAVE A REPLY