ኤጀንሲው ለእናቶችና ለሕፃናት የሚሆኑ መድኃኒቶችን እያከፋፈልኩ ነው አለ

ኤጀንሲው ለእናቶችና ለሕፃናት የሚሆኑ መድኃኒቶችን እያከፋፈልኩ ነው አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለቤተሰብ ምጣኔ እንዲሁም ለእናቶችና ሕፃናት የሚሆኑ  መድኃኒቶችን እያሰራጨሁ ነው ብሏል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 1.1 ቢልየን ብር በላይ ወጪ ያላቸውን የቤተሠብ ምጣኔ እንዲሁም የእናቶችና ሕፃናት ግብዓቶችን ለሕክምና ተቋማት ማከፋፈሉን የገለጹት በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ባለሙያ አቶ አድማሱ ውብአንተ አስታውቀዋል።
ኤጀንሲው ግብዓቶቹን ባሉት 18 ቅርንጫፎች በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ የጤና ተቋማት ማሰራጨቱን፤ በተጠቀሱት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ1 ቢልየን 134 ሚሊየን በላይ የቤተሠብ ምጣኔ እና የእናቶችና ሕፃናት ግብዓቶች እንዲከፋፈሉ አድርጓል።
ኤጀንሲው ለህክምና ተቋማቱ ከሚያከፋፍላቸው መድኃኒቶች መካከልም ልዩ ልዩ የቤተሠብ ምጣኔ ግብዓቶች፣ ለነፍሠ ጡር እናቶች የሚውል አይረን እና ፎሊክ አሲድ፣ ለሕፃናት የሚሆን አልቤንዳዞል  እንዲሁም ለእናቶች፣ ሕፃናትና ጨቅላ ሕፃናት አገልግሎት የሚውሉ ምርቶች ቀዳሚዎቹ መሆናቸውንም አረጋግጧል።

LEAVE A REPLY