እምቦጭ ላይ እርምጃ ያልወሰደው የአማራ ክልል 1 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተዘጋጅቻለሁ አለ

እምቦጭ ላይ እርምጃ ያልወሰደው የአማራ ክልል 1 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተዘጋጅቻለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በመጪው ክረምት ወር ለሚተገበረው የጠቅላይ ሚኒስትሩ 5 ቢሊዮን የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት ችግኞች፣ 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ተዘጋጅቻለሁ አለ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳ አየሁ፤ ክልሉ ለችግኝ ተከላ፣ የቅድመ ዝግጅት ሥራው ያለፈው ዓመት ችግኝ ተከላ እንደተጠናቀቀ የተጀመረ መሆኑን አስታውሰው፤ በቅድመ ዝግጅት ሥራው ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ተግዳሮቶችና ስኬቶች ላይ ግምገማ በማድረግ እንቅፋቶችን ለማስወገድ  ሢሠራ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታና ከፍተኛ የመፅደቅ መጠን ያላቸውን ችግኞች ለመትከል እስካሁን 1 ነጥብ 28 ቢሊየን ችግኝ ተቆጥሮ መዘጋጀቱን፣ እንዲሁም ለደንና ለጥምር ደን የችግኝ ተከላ የሚሆን 164 ሺህ ሄክታር መሬት ቦታ ተዘጋጅቷል መዘጋጀቱ ተነግሯል።
በጣና ሐይቅ ላይ ችግር የፈጠረውና በቀጣይም በሌሎች ተዛማጅ ሐይቅና ወንዞች ላይ ከባድ ጥፋት እያደረሰ ያለውን የእምቦጭን አረም መቆጣጠር ያልቻለውና ትኩረት የነፈገው የአማራ ክልል ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ ችግኞችን ለማፍላት መጣደፉ ብዙዎችን አስገርሟል።

LEAVE A REPLY