የአፍሪካ ቀን ዛሬ በመላ አህጉሪቱ ታስቦ ዋለ

የአፍሪካ ቀን ዛሬ በመላ አህጉሪቱ ታስቦ ዋለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– እንደ አውሮፓውያኑ የቀን አቆጣጠር በየዓመቱ ግንቦት 25 የሚከበረው የአፍሪካ ቀን ዛሬም በመላው አህጉሪቱ እየታሰበ ነው።

ቀደም ሲል በአፍሪካ ኅብረት በተለያዮ ፕሮግራሞች ሲከበር የቆየው በዓሉ ዛሬ ቪዲዮ በሚካሄድ  እንደሚታሰብ የጠቆመው ኅብረቱ፤ በቪዲዮ ኮንፍረንሱ “የቫይረሱን ድምፅ ማጥፋት” ሚለውን የዘንድሮው የኀብረቱ መሪ ቃል ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር አስተሳስሮ ይወያይበታል ተብሏል።
በኮቪድ-19 ምክንያት በዓላትን ማዘጋጀት ባለመቻሉ በሚደረጉ የቪዲዮ ኮንፈረንሶች ላይ የዘንድሮውን መሪ ቃል በዚህ የወረርሽኝ ወቅት እንዴት ማሳካት ይቻላል በሚለው ላይ እንደሚመክርና፤ ከዛሬው በተጨማሪ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ሌሎች ፕሮግራሞች እንደሚዘጋጁ በመግለጫው ላይ ይፋ አድርጓል።
“በብዙ ጸጋ የታደለችው፣ ሁሉም ዓይነት ብዝኃነት የሞላባት አህጉራችን መድረሻዋ መልከ ብዙ ብልጽግና ነው” ሲሉ ለበዓሉ መልእክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ዛሬ የአፍሪካ ቀንን ስናከብር የምንፈልጋትን አፍሪካ እውን ለማድረግ፣ አንድነታችንን ማጠንከር ይኖርብናል በማለት ምክር ለግሰዋል።
የአፍሪካ ቀን ሲታሰብ በተለይ ለአፍሪካ ህብረት መመስረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ያደረጉት ጉልህ ሚና ተጠቃሽ ነው።

LEAVE A REPLY