በአቋማሪነት 6 ቢሊየን ዶላር ያካበቱት “የቁማሩ ጌታ” በ98 ዓመታቸው ሞቱ

በአቋማሪነት 6 ቢሊየን ዶላር ያካበቱት “የቁማሩ ጌታ” በ98 ዓመታቸው ሞቱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– “የቁማሩ ጌታ” በመባል የሚታወቁት ቢሊየነሩ ስታንሊ ሆ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተነገረ።

በደቡብ ቻይና ጠረፍ የምትገኘው “ማካዎ” የተሰኘችው ከተማን የዓለም የቁማር ማዕከል ያደረጓት እኚህ ሀብትና ዝናቸው የገዘፈው አቆማሪ በ98 ዓመታቸው ነው የሞቱት።
ማካዎ ከተማን ከመሰረቷትና የቁማር መናኸሪያ ያደረጓት “የቁማሩ ጌታ” ቀስ በቀስ እሲያ አህጉር ካሉ ከእውቅ ሀብታሞች ተርታ ሊመደቡ ያስቻላቸውን ሀብት ያጋበሱትም ከዚሁ ሥራ ጋር በተያያዘ ሲሆን፤ ዓለም ላይ ዝናው የናኘው፤ ኤስ ኤም ጂ ሆልዲንግስ የተባለውን ትልቁን አቋማሪ ድርጅት የመሰረቱትም አርሳቸው እንደሆኑ ግለ ታሪካቸው ያሳያል።
በፈረንጆቹ በ2018 አዛውንቱ ባለሀብት ከአቋማሪነት ሥራቸው ጡረታ ሲወጡ የስታንሊ ሆ ሀብት 6.4 ቢሊየን ዶላር አልፏል።
ስታንሊ ሆ በዚያች  ከተማ ብቻ 20 የካዚኖ ማስቆመርያ ድርጅቶች ያሏቸው ሲሆን፤ ድርጅታቸው በቻይና ውስጥም በሌሎች የንግድ ዘርፎች ከፍተኛ ትርፍ እያስመዘገበ ይገኛል።
ቢሊየነሩ ስታንሊ ሆ የእኔ ብለው የተቀበሏቸው 17 ልጆች ሲኖሯቸው፣ በይፋዊ ጋብቻ ሥነ ሥርዓት  አራት ሚስቶችን እንዳገቡ የዘገቡት የቻይና ሚዲያዎች፤ የሆን ሞትን  “የጀግናው ቢዝነስ ሰው ሞት” ሲሉ ነበር የዘገቡት።

LEAVE A REPLY