በጋምቤላ ከዓመታት በፊት በነበሩ ግጭቶች ለተፈናቀሉ 600 ሰዎች ድጋፍ ተደረገ

በጋምቤላ ከዓመታት በፊት በነበሩ ግጭቶች ለተፈናቀሉ 600 ሰዎች ድጋፍ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለነበሩና በቅርቡ ወደ ቀያቸው ለተመለሱ 650 አባዎራዎችና እማዎራዎች  ድጋፍ ተደረገ።

ቀደም ሲል በነበሩት ዓመታት በነበሩ ግጭቶች ቀዬአቸውን ለለቀቁ ተፈናቃዮች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን የገለጸው የጋምቤላ ብዙሃን መገናኛ  ኤጀንሲ፤ ድጋፉ የተገኘው  ዩኤን ኤችሲአር (UNHCR) ከተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ሲሆን፤ ድጋፉን በማስተባበሩ ረገድ አይ አር ሲ (IRC) ተብሎ የሚጠራው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ከፍተኛ ድርሻ አለው ብሏል።

የኢታንግ ልዩ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኦኬሎ ኡባንግ እርዳታው የኮቪድ 19 ቫይረስ በኅብረተሰቡ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተፅዕኖ ለመቀነስና ለመከላከል እየተደረገ ባለው የሀብት ማሰባሰብ ተግባር ከለጋሽ ድርጅቶች የተገኘ መሆኑን ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY