የህዳሴው ግንባታ የተፋሰሱን ሀገራት አይጎዳም ሲል የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ገለፀ

የህዳሴው ግንባታ የተፋሰሱን ሀገራት አይጎዳም ሲል የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የተፋሰሱን አገራት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያስጠብቅ እንጂ የሚጎዳ አለመሆኑን የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ   ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ አድርጓል።

የሃይማኖት ተቋማቱ የበላይ ጠባቂዎች በጋዜጣዊ መግለጫው የወቅቱ የዓለም የጤና ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ፈጣሪ በምህረቱ እንዲያጠፋው ከመጠየቃቸው ባሻገር መግለጫውን በጸሎት ጀምረዋል።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የዓይን ብሌን ነው ያሉት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ግድቡ ለተፋሰስ ሀገራቱ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም ብለዋል።
ሼህ ቃሲም ሼህ መሐመድ ታጅዲን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ እና የቀዳሚ ሙፍቲ ተወካይ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ የአባይን ወንዝ ግድብ ለመጠቀም የምታደርገው እንቅስቃሴ ተፈጥሯዊ መብቷ ነው ከማለታቸው ባሻገር፤ “በግድቡ ዙሪያም ያስቀመጠችው ፍትሃዊ ድርድር በእስልምና እምነት አስተምሮም ተቀባይነት ያለው ስለሆነ የሃይማኖት ተቋማት በግድቡ ዙሪያ ያላቸውን የአንድነት አቋም አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል”  ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአባይ ወንዝ የታችኞቹ ተፋሰስ አገራት የውሃና የስልጣኔ ምንጭ እንደመሆኑ የአንድ ወገን ፍትህዊ ያልሆነ ተጠቃሚነት አግባብ የሌለው መሆኑን የገለፁት  ብፁዕ ካርዲናል ብርነ ኢየሱስ ጳጳሳት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊያን ቤተ ክርስትያናት ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት፤ መንግሥት እየሄደበት ያለው አቋም ትክክለኛ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY