ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ላለፉት 24 ሰዐታት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሠላሳ ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 30 ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ በፆታ ረገድ 23 ወንዶች እና 8 ሴቶች መሆናቸውን ያስታወቀው የጤና ሚኒስቴር፤ ዕድሜያቸው ከ9 እስከ 60 የሚደርስ መሆኑንም አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 731 መድረሱምን መግለጫው ያስረዳል።
ከዛሬ አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከሆኑት 30 ሰዎች ውስጥ 11 የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 5 በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው፣ 14ቱ ደግሞ የጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው እንደሆኑ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል 14 ሰዎች ከአዲስ አበባ ያገገሙ መሆናቸውን ተከትሎ  በአጠቃላይ ያገገሙት ቁጥር 181 መድረሱን ያመላከተው መግለጫ፤ 30 ዎቹ የኮቪድ 19 ቫይረስ ተጠቂውች የተገኙት ከአዲስ አበባ (15)፣ ከትግራይ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው (2)፣ ከአማራ ክልል ሁሉም የጉዞ ታሪክ ያላቸው (8)፣ ከሀረሪ ክልል (3)፣ ከኦሮሚያ ክልል(1)፣ ድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ (1) እንደሆኑ ያስረዳል ።

LEAVE A REPLY