ከ219 ሺኅ በላይ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶችን ከጎዳና ሊነሱ ነው 

ከ219 ሺኅ በላይ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶችን ከጎዳና ሊነሱ ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከኤልሻዳይ ሪሊፊና ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን ጋር በመሆን ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶችን ለማንሳት የሚያስችል መርሃግብር ለመጀመር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረሙ ተነግሯል።

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ፤ መ/ቤታቸው ቀደም ባለው ጊዜ ከኤልሻዳይ ጋር በመሆን በጎዳና ላይ የሚገኙ ህጻናትንና ልጆች ይዘው በጎዳና ላይ የሚኖሩ ወላጆች ከጎዳና እንዲነሱ የስነልቦና እና የምክር አገልግሎት እንዲያገኙና የክህሎት ስልጠና ወስደው እድሜያቸው በሚፈቅደው የገቢ ማስገኛ ዘርፎች እንዲሠማሩ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ይህንን በጎ ተሞክሮ አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችል ዘንድ ከኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት ጋር በመተባበር ከ219 ሺኅ በላይ የሚሆኑ የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች በቀጣይ ሦስትና አራት ዓመታት ውስጥ ከጎዳና ለማንሳት መታቀዱ የመግባቢያ ሰነዱ ሲፈረም ተገልጿል።
በኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ቅድስት፣ ከዚህ በፊት ከ122 ሺኅ በላይ ዜጎችን ከልመናና ጎዳና ሕይወት ተላቀው እንዲወጡ ለማድረግ መቻላቸውን አስታውሰው፣ ለሥራቸው መሳካት ድጋፍ ላደረጉላቸው የመንግሥት አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አዲስ በተፈረመው መግባቢያ ሰነድ መሠረት በመጀመሪያ ዙር  20 ሺኅ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ከጎዳና ላይ በማንሳት በማዕከሉ ለዘጠኝ ወራት የሚቆዩ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ሦስት ወር የሥነ ቦና ስልጠና ይሰጣቸዋል፤ በቀጣይቹ ስድስት ወራት  የክህሎት ስልጠና በመስጠት ራሳቸውን በኢኮኖሚ እንዲደግፉና ወደ ማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ ይደረጋል ተብሏል።

LEAVE A REPLY