በኢትዮጵያ ሠባተኛ ሰው ሞተ፣ 100 አዲስ የኮሮና ተጠቂዎችም ተገኙ

በኢትዮጵያ ሠባተኛ ሰው ሞተ፣ 100 አዲስ የኮሮና ተጠቂዎችም ተገኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ 4.950 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ (100) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ገለፀ፡፡

ይህን ተከትል በኢትይጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ (831) ደርሷል፡፡
 ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች እድሜያቸው ከ3 እስከ 70 ዓመት ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፤  53ቱ ወንድ፣ 47ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡ ከመቶዎቹ ሰዎች መሀል 99 ሰዎች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ፣ 1 ሰው የቡሪንዲ ዜግነት እንዳለው ከመግለጫው መረዳት ተችሏል።
ዛሬ ይፋ ከተደረጉትና ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መሀል 94 ሰዎች ከአዲስ አበባ መሆናቸው ታውቋል። ከእነርሱም መሀል 34 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ሲኖራቸው ፤ 60ዎቹ ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ወይም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው እንደሆኑም ተነግሯል።
አንድ ሰው ከትግራይ ክልል የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ፣ ሁለት ሰዎች ከሶማሌ ክልል ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ያሉ፣ እንዲሁም 3 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ሲሆኑ፣ አንድ ሰው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለውና 2ቱ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው ናቸው እንደሆነ የጤና ሚኒስትር ይፋ አድርጓል።
በተያያዘ ዜና በሌላ ሕመም ምክንያት ሕክምና ላይ የነበሩ የ70 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት፤ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ በተደረገ ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤት ሳይደርስ ህይወታቸው ቢያልፍም፣ በናሙናው ውጤት ቫይረሱ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን ተከትሎ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባት (7) መድረሱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY