የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ፣  2 ቢሊየን ችግኞችን እተክላለሁ አለ

የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ፣  2 ቢሊየን ችግኞችን እተክላለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሁለት ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል በዝግጅት ላይ ነኝ ሲል ገለፀ።

ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀን የሚቆይ  የሴቶች ሊግ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ እያካሄደ የሚገኘው ፓርቲው የተለያዩ መርሃ ግብሮችን እያካሄደ ሲሆን፤ በመጪው ክረምት ወራት ሁለት ቢሊዮን በሊጉ አማካይነት ለመትከል አቅጃለሁም ብሏል።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽ/ቤት ሓላፊ ወ/ሮ መስከረም አበበ፤ ባለፈው ዓመት በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮጀክት የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስታውሰው፤ በያዝነው ዓመትም ሁለት ቢሊየን ችግኝ ለመትከል በዝግጅት ላይ ነን ሲሉ ተደምጠዋል።
ከኢህአዴግ ሊግ ወደ ብልፅግና ሊግ የዞረው የሴቶቹ ስብሰብ፤  ባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራ ከመሥራት ባሻገር፤                                                           ሴቶች በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንዳይሆኑ የተለያዩ ሥራዎችን ጎን ለጎን እያካሄድን ነው በማለት ገልጿል።  በተለያዩ ደረጃ ለሚገኙ ሴቶችም ድጋፍ እየተደረገ ነው ማለታቸውን የመንግስት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

LEAVE A REPLY