የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው የማግለል ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው የማግለል ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በዚህ ፈታኝ ወቅት በኢትዮጵያ ወጭና ገቢ ንግድ ሎጀስቲክስ አገልግሎት ላይ ትልቁን ሚና እየተወጡ ለሚገኙ የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ኅብረተሰቡ ድጋፍና ትብብር ሊያደርግ ይገባል ተባለ።

የኮሮና ቫይረስ መስፋፋቱ፣ በአጎራባች አገሮች ቫይረሱ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ ድንበር ተሻጋሪ የጭነት አሽከርካሪዎች ላይ መገለል እየደረሰባቸው መሆኑ ሰሞኑን በስፋት እየተነገረ ይገኛል።
ራሳቸውን ለኮሮና ቫይረስ የበለጠ አጋልጠው እየተንቀሳቀሱና ሙያዊ ግዴታቸውን እየተወጡ መሆኑን ያስታወሰው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር፤ በድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ላይ የሚስተዋለውን የመገለል ችግር ለመፍታት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ጀምሪያለሁ ብሏል።
ወቅታዊ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራው በድሬዳዋ ከተማ የተጀመረ ሲሆን፤ በአይሻ ደወሌ መስመር እስከ ጅቡቲ በሚያዘልቀው መስመር ላይ በቀጣዮቹ ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና፤ በቅስቀሳውም በአገሪቱ በወጭና ገቢ ሎጀስቲክስ አገልግሎት የተሰማሩ የጭነት አጓጓዥ አሽከርካሪዎችን ማኅበረሰቡ ክብር በመስጠትና በማገዝ እንዲተባበራቸው መልዕክት ተላልፏል።
እነዚህ መገለልና መድልዎ እየተፈጸመባቸው ያለው ድንበር እያቋረጡ የግብርና፣ ኢንዱስትሪና የግንባታ ግብዓቶችን በማመላለስ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በማንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት አሽከርካሪውች፤ እየፈጸሙት ያለው ሚናም ከፍተኛ ነው ተብሏል።

LEAVE A REPLY