የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ተጀመረ 

የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ትምህርት ማስጨረስ ተጀመረ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መደበኛ የትምህርት ሂደቱ ቢቋረጥም፤ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተሰምቷል።

የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ተቋሞቻቸው የሚላኩላቸውን የትምህርት ሰነዶች እያነበቡ እንዲቆዮ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ተላልፏል።
እንደወትሮው የምረቃ ሥነ ሥርዓት ባይኖርም አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ እንደጀመሩ ታውቋል።
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው፣ እንዲሁም በተማሪውና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ ነው የተነገረው።
የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፤ በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ (ሴሚስተር) ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት ላይ እያሉ ወረርሽኙ በመከሰቱ ምክንያት ባለመፈተናቸው፣ በያዝነው ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች እንደማይኖሩም ታውቋል።

LEAVE A REPLY