ግንቦት 20 ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚበልጥ ሙስጠፌ መሐመድ ተናገሩ

ግንቦት 20 ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚበልጥ ሙስጠፌ መሐመድ ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ግንቦት 20 ለሶማሌ ክልል ህዝብ ካስገኘለት ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን፣ አምባገን ሥርዓቱ በክልሉ ህዝብ ላይ በታሪኩ ተፈፅሞበት የማያውቀው ግፍና በደል እንዳደረሰ አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ገለፁ።

ግንቦት 20 ለሶማሌ ክልል ህዝብ በቋንቋው ከመማርና ራስን በራስ ከማስተዳደር መብት ካስገኘለት ጥቅም ይልቅ በከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መጥፎ አሻራ ማሳረፉንም መስክረዋል።
የሶማሌ ክልል ሕዝብ በግንቦት 20 ካገኘው ጥቅም ይልቅ በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በውሸት ፌዴራሊዝምና እና በሀብት ዘረፋ ከደረሰበት የከፋ በደል የተነሳ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ያሉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር፤ በህወሓት የተመራው ሥርዓት በሶማሌ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሥነ ልቦናዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መጥፎ አሻራ ማሳረፉን መቼም አንረሳውም ብለዋል፡፡
ህወሓት በአገር ዐቀፍ ደረጃ ሲያራምድ የነበረው ሕዝብን ከሕዝብ የማናከስና የጥላቻ ፖለቲካ እንደነበር ያስታወሱት ሙስጠፌ፤  ሥርዓቱ በሶማሌ ህዝብ ላይ በታሪኩ ተፈፅሞበት የማያውቀው ግፍ፣ ግድያ፣ ማንገላታት አድርሶበታል፤ በተደራጀ መልኩ ሕዝባችነን የማዋራድ ሥራ ተሠርቷል ሲሉ ግንቦት 20 ይዞት የመጣውን እዳ አመላክተዋል።
“የሶማሌ ክልል አሁን ባለው ለውጥ ደስተኛ ነው፤ የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ በኮንትሮባዲስቶችና በእነሱ ኔት ወርኮችና ተጠቃሚዎች አማካኝነት የሚሞከሩ አፍራሽ ሥራዎች ቢኖሩም የክልሉ ተቋማት በተካሄዱት የሪፎርም ሥራዎች ጠንካራ በመሆናቸው፤ ችግሮቹን አስተማማኝ በሆነ መልኩ መመከት የሚያስችል አቅም መፍጠር ችለናል” ብለዋል።

LEAVE A REPLY