ለያዝነው 2012 በጀት ዓመት 48.3 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ፀደቀ

ለያዝነው 2012 በጀት ዓመት 48.3 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት ፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አምስተኛ ዓመት 4ኛ ልዩ ስብሰባ እያገባደድነው ላለው 2012 ዓ.ም ተጨማሪ 48.3ቢሊዮን ብር አፅድቋል።

በተጨማሪ በጀትነት ከፀደቀው 48.3 ቢሊየን ብር ውስጥ 28.3 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ አገራት፣ እንዲሁም 20 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ከሀገር ውስጥ የሚገኝ እንደሆነም ተገልጿል።
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በጉዳዮ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ  ተጨማሪ በጀቱ የኮሮና ወረርሺኝ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያለመ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ ለተጨማሪ በጀቱ ከውጭ የሚገኘው ብድር የዋጋ ንረትን እንዳያስከትል ጥንቃቄ የተሞላበት የብድር ሂደት እንከተላለን በማለት መንግሥት ጥንቃቄ እንደሚያደርግም አብራርተዋል።
ለፌዴራል መንግሥት የ2012 በጀት ዓመት 386.9 ቢሊዮን ብር ሆኖ ባለፈው ዓመት መፅደቁ ይታወሳ

LEAVE A REPLY