ምርት ገበያ 30.4 ቢሊዮን ብር በማገበያየት እቅዴን አሳክቻለሁ አለ

ምርት ገበያ 30.4 ቢሊዮን ብር በማገበያየት እቅዴን አሳክቻለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኮሮና ቫይረስ ዓለም ላይ ስጋት በርካታ የንግድና ኢንዱስቴሪ ምርቶች ለኪሳራ እየተዳረጉ ባለበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለፉት ወራተ ስኬታማ ጉዞ አድርጊያለሁ ብሏል።

በጉዳዮ ላይ ማብራሪያ የሰጠው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 602,823 ቶን ምርት በ30 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በማገበያየት የእቅዴን 97 በመቶ አሳክቻለሁ ሲል ገልጿል።
ድርጅቱ ለአዲስ ማለዳ እንደገለፀው ከሆነ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 231 ነጥብ 885 ቶን ቡና፣ 211 ነጥብ 772 ቶን ሰሊጥ፣ 69 ነጥብ 760 ቶን አኩሪ አተር፣ 46 ነጥብ 914 ቶን አረንጓዴ ማሾ፣ 39 ነጥብ 286 ቶን ነጭ ቦሎቄ እና 3 ነጥብ 201 ቶን ቀይ ቦሎቄ ለገበያ አቅርቧል።

LEAVE A REPLY