ቀነኒሳ እና ኪፕቾንጌ በበይነ መረብ በሚካሄድ የማራቶን ውድድር ላይ ይሳተፋሉ ተባለ

ቀነኒሳ እና ኪፕቾንጌ በበይነ መረብ በሚካሄድ የማራቶን ውድድር ላይ ይሳተፋሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የዓለም የአትሌቲክስ ፈርጥ የሆኑት ቀነኒሳ በቀለ፣ ኢሉድ ኪፕቾጌ፣ ጆሽዋ ቼፕቴጌ፣ ጂዮፌሪ ካማዎሮር በሚቀጥለው ወር በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በሚከናወነው ምናባዊ ማራቶን (የበይነ መረብ ማራቶን) እንደሚሳተፉ ተረጋገጠ።

የማራቶን ውድድሩ እኤአ ሰኔ ሥድስት እና ሰባት ቀን 2020 የሚካሄድ እንደሆነና የአትሌቲክስ ወዳጆችና አድናቂዎች በሙሉ ሊሳተፉበት እንደሚችሉ ተገልጿል።
የበይነ መረብ ሩጫው ሐሳብ አመንጪ ኤን.ኤን የሩጫ ቡድን፣ ውድድሩ የምናብ ሩጫ፤ በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች አራት በመሆን ቡድን መስርተው፣ የማራቶንን ርቀት የሚሸፍኑበት ነው ብሏል።
“አንድ ግለሰብ ባለበት ቀዬ 10.5 ኪ.ሜ መሮጥ ይኖርበታል። አጋሮቹም ይህንን ያደርጉና ሙሉ ማራቶን ይሞላል። ይህ የሆነው ሯጮች ከንክኪ ውጭ በያሉበት ሥፍራ ማራቶን እንዲሳተፉ ለማስቻል ነው” ያሉት አዘጋጆቹ፤ ሁሉም ነገር በበይነ-መረብ አማካይነት ይመዘገባል ሲሉም ገልጸዋል።
 “እኔና የቡድን አባላቶቼ ሩጫውን ለመቀላቀል በጉጉት እየጠበቅን ነው” ያለው ኪፕቾንጌ ፤ ወቅቱ ሁሉም ሯጮች እቅዳቸውን መለስ ብለው የሚከልሱበት መሆኑን ጠቁሞ፤ “መጻኢው ጊዜ መልካም እንደሚሆን እምነት አለኝ፣ ይህም ወደ በጎ ነገር የሚወስደውን አንዱ እርምጃ ነው። ማራቶን እውቅ ስፖርተኞች እንዲሁም ስፖርት ወዳድ ማኅበረሰብ አባላት በጋራ የሚሮጡበት መስክ ነው” ሲል ሐሳቡን ገልጿል።

LEAVE A REPLY