“አልቃድሪፍ” ላይ የኢትዮጵያና የሱዳን ታጣቂዎች ከባድ ጦርነት እያደረጉ መሆኑ ተሰማ

 “አልቃድሪፍ” ላይ የኢትዮጵያና የሱዳን ታጣቂዎች ከባድ ጦርነት እያደረጉ መሆኑ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከጥቂት ወራት ወዲህ በአባይ ጉዳይ ወጥ አቋም መያዝ ያቃታት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በድንበር አካባቢ ጦርነት ከፍታለች ነው የተባለው።

በሱዳን ጦር እና የኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል “አልቃድሪፍ” በተሰኘው አካባቢ ከባድ ጦርነት መጀመሩን አረጋግጫለሁ ሲል የዘገበው ዓለም ዐቀፉ የዜና አውታር ሮይተርስ ነው።
ከረቡዕ ዕለት ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሱዳን ጦር እና ኢትዮጵያ ታጣቂዎች መካከል ድንበር ላይ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑን የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል አሚር መሃመድ አል ሐሰንም እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ ይህን የተናገሩት በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ቀርበው በድንበር አካባቢው በሁለቱ ሀገር ታጣቂዎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ ነው ያሉ ሲሆን “ለታጣቂዎቹ የኢትዮጵያ ጦር ድጋፍ እያደረገላቸው ነው” ሲሉም ወቅሰዋል።
በድንበር አካባቢ በተደረገው ውጊያ አንድ የሱዳን ጦር መኮንን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች መገደላቸው እና መቁሰላቸውን የዘገበው ሮይተርስ፤ ውጊያው እየተካሄደ ያለው አልቃድሪፍ ተብሎ በሚጠራው ድንበራማ አካባቢ ሲሆን፣ በዚህ ስፍራ በእርሻ መሬት የተነሳ ተደጋጋሚ ግጭቶች እንደሚካሄድበት ይታወቃል።

LEAVE A REPLY