በመቀሌ አንዲት ሴት በጥይት ተመትታ መሞቷ ታወቀ

በመቀሌ አንዲት ሴት በጥይት ተመትታ መሞቷ ታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል፣ መቀለ ከተማ አንዲት ሴት ከታጣቂ ሚሊሻ በተተኮሰባት ጥይት መገደሏ ተነገረ።

በመቀሌ ከተማ ትናንት ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት ላይ ነው ግለሰቧ በጥይት ተመትታ ሕይወቷን ያጣችው።

ሴትዮዋ ከታጣቂ ሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት መገደሏን የመቀሌ ከተማ ወንጀል መከላከልና ምርመራ ጽ/ቤትም እማኝነቱን ሰጥቷል።
ፖሊስ እንደገለፀው ከሆነ በስም ያልተጠቀሱት ሁለቱ ግለሰቦች በሥራ ክፍያ ሳይስማሙ ቀርተው አለመግባባታቸው በመባባሱ ታጣቂው ሚሊሻ ጥይት ተኩሶ ሴትዮዋን ገድሏታል።
ታጣቂው በተኮሰባት ጥይት የተመታቸው ሴት፤ ህይወቷ ወዲያውኑ አልፏል ያለው የመቀሌ ከተማ ፖሊስ፤ ታጣቂው ግድያውን ከፈፀመ በኋላ ራሱ ላይ በመተኮሱ ለጉዳት በመዳረጉ፣ ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዶ፣ በሆስፒታሉ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለት በፖሊስ ጥበቃ ሥር ሆኖ ሕክምናውን በመከታተል ላይ ነው ሲል አስታውቋል።

LEAVE A REPLY