ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ5.034 (አምስት ሺኅ ሠላሣ አራት) ሰዎች በተደረገ ላብራቶሪ ምርመራ 95 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ሚንስትር አስታወቀ።
ይህን ተከትሎ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1.063 (አንድ ሺኅ ስልሳ ሦስት) ደርሷል።
በአንፃሩ ትናንት ከአዲስ አበባ 11 ሰዎች፤ 2 ከትግራይ ክልል እና 9 ከአፋር ክልል ከበሽታው በማገገማቸው ። እስካሁን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 208 ደርሷል፡፡
የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ በተለይም በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን የገለፀው የጤና ሚኒስቴር አምስት ሰዎች በፅኑ ሕክምና መስጫ ውስጥ እንደሚገኙም ይፋ አድርጓል፡፡