ዝናብ በሚያስከትለው የጎርፍ አደጋ የኮቪድ 19 ቫይረስ ሊባባባስ ይችላል ተባለ

ዝናብ በሚያስከትለው የጎርፍ አደጋ የኮቪድ 19 ቫይረስ ሊባባባስ ይችላል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በበሀገሪቱ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የዝናብ ስርጭት በሚያስከትለው የጎርፍ አደጋ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳይባባስ ተጋላጭ የሆኑ ተፋሰሶች የቅድመ መከላከል ስራቸው በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ታዘዘ።

የተፋሰሶች ከፍተኛ ምክር ቤት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ሲካሄድ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት እና የቅድመ መከላከል ሥራዎችን በፍጥነት ማከናወን እንደሚገባ ጠቁመው፤ በጎርፍ ምክንያት የሚከሰተው አደጋ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት የተጀመረውን ሀገራዊ ጥረት በእጅጉ እንደሚፈታተነውም ገልፀዋል።
“ከፊት ለፊት የሚገጥሙ ውስብስብ ችግሮችን አስቀድሞ በቅድመ መከላከል ሥራዎች በሚገባ መመከት የሚቻልበትን አቅም ሙሉ በሙሉ በመጠቀም፣ የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ጎን ለጎን ማጎልበት ይገባልም” ሲሉ አሳስበዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የቅድመ መከላከል ሥራዎች መካከል የወንዝ አቅጣጫ አመራር እና የጎርፍ መከላከል ዳይክ ሥራና ጥገና እየተካሄደ መሄዱን የጠቆሙት የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፤ የተጠናከረ የግድብ አስተዳደር እና የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን ደረጃ የማሳደግ ሥራዎችም በፍጥነት በመከናወን ላይ ናቸው በማለት ገልፀዋል።
ከክረምቱ መቃረብ፣ ከኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ማድረግ አኳያ፤ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ የጎርፍ ስጋት የተደቀነባቸውን አካባቢዎች ቅድሚያ በመስጠት፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ የቅድመ መከላከል ሥራዎች እንዲጠናቀቁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።

LEAVE A REPLY