ሲጋራ ላይ እጥፍ ዋጋ የጨመረችው ኢትዮጵያ፣ የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀንን አከበረች

ሲጋራ ላይ እጥፍ ዋጋ የጨመረችው ኢትዮጵያ፣ የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀንን አከበረች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በዓለም ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ ዛሬ ተከበረ።

በየዓመቱ ግንቦት 23 በሚከበረው ትንባሆ የማይጨስበት ቀን፤ በተለይም ወጣቱ ትውልድ የትምባሆ ኢንዱስትሪ ከሚፈጥረው ተፅዕኖ ራሱን እንዲቆጥብ፣ ብሎም ገዳይነቱን በመገንዘብ ትምባሆ እና ኒኮቲን ከሚያስከትሏቸው የጤና ጠንቆች ራሱን እንዲጠብቅ የዓለም ጤና ጥሪ መልዕክት አስተላልፏል።
በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የሚከበረው የዘንድሮው የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን “ወጣቶችን ከኢንዱስትሪ ተፅዕኖ በመከላከል፣ ከትምባሆ እና ኒኮቲን ጠንቆች እንጠብቃቸው!” የሚል መርህ የያዘ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ደግሞ “የትምባሆ ምርቶችን ባለመጠቀም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጉዳት እንከላከል!” በሚል መሪ ሐሳብ መከበሩን መረዳት ተችሏል።
ሲጋራ እና ሺሻ የሚያጨሱ ሰዎች ለኮሮናቫይረስ ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለሥልጣን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከመግባቱ አስቀድሞ  የሲጋራ አጫሾችን ለመቀነስ አንድ ብር የነበረውንና ብዙ ተጠቃሚ ያለውን “ኒያላ” የተሰኘውን ሲጋራ 1ብር ከሃምሳ ሳንቲም እንዲሸጥ አድርጋ ነበር።
ሆኖም የተጠቃሚው ቁጥር ባለመቀነሱ፣ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትም በኢትዮጵያ በመባባሱ አንድ ኒያላ ሲጋራ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ 2ብር ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ ሲሆን፣ በአንዳንድ ሱቆች አንዷ ሲጋራ በሦስት ብር የምትሸጥበት ሁኔታ መኖሩንም ተመልክተናል።

LEAVE A REPLY